JavaScript is required

የቪክቶሪያ የፀረ ዘረኝነት ስትራቴጅ 2024–2029 (Victoria's anti-racism strategy 2024-2029) - አማርኛ (Amharic)

ቪክቶሪያ ውስጥ የመጀመሪያው እና አጠቃላይ የመንግስት የፀረ-ዘረኝነት ስትራቴጂ በቪክቶሪያ ዘረኝነትን እና መድሎን ለማስቆም የሚያስችል የ5 ዓመት እቅድ ነው።

Victoria's anti-racism strategy in Amharic
PDF 1.17 MB
(opens in a new window)

አብረን በመሥራት ሁሉንም አካታች የሆነ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቪክቶሪያን መገንባት እንችላለን።

ዘረኝነት ምንድን ነው?

ዘረኝነት ማለት ሰዎች በማንነታቸውን ወይም በዘራቸውን ምክንያት የሚደርስባቸ አድልዎ እና በደል ነው። ማንቋሽሸን (ስድብን)፣ ማግለልን ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል የሆነ አጋጣሚ ወይም እድል አለመስጠትን ሊያካትት ይችላል።

ዘረኝነት በብዙ መንገዶች ሊከሰት ይችላል። ይህ ስትራቴጂ የሚያተኩረው ዘረኝነት በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ሲከሰት ለመቅረፍ ነው፡

  • በማህበረሰቡ ውስጥ
  • በድርጅቶች እና በተቋማት ውስጥ
  • በህጎች፤ በፖሊሲዎች እና በስርዓቶች ውስጥ።

ራእያችን

ከዘረኝነትና ከአድልዎ ነጻ የሆነች ቪክቶሪያን መፍጠር። የዚህ መገለጫው ሁሉም ቪክቶሪያዊያን እኩል መብት፣ ነጻነትና ጥበቃ የሚያገኙበትና አስተማማኝ፣ ጤናማና ደጋፊ የሆኑ ማህበረሰቦች መገንባት ይሆናል።

ይህ ስትራቴጂ በቪክቶሪያ ውስጥ ዘረኝነትንና አድልዎ የመድረስ እድልን ለመቀነስ የሚያስችሉ 4 ግቦች አሉት፡

  • ግብ 1፡የዘረኝነት አመለካከቶች፣ ባህሪያት እና እምነቶች ተለይተው ከታወቁ በኋላ እነዚህ ችግሮች ሲታዮ ትክክል እንዳልሆኑ ማሳወቅ እና ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ማድረግ።
  • ግብ 2፡የመንግስት አገልግሎቶች እና የስራ ቦታዎችን ለደህንነት አስተማማኝ፣ ተደራሽ እና ከአድልዎ የጸዱ ማድረግ።
  • ግብ 3፡ ዘረኝነት እና አድልዎ በሁሉም ዘርፎች ላይ በሰዎች ተሳትፎ፣ እድገት፣ ደህንነት እና ስኬት ላይ እንቅፋት መሆኑ ማስቀረት።
  • ግብ 4፡ ለዘረኝነት እና ለአድልዎ ለተጋለጡ ሰዎች ተገቢ እና የተጠቂውን ሰው ባህል ግምት ውስጥ ያስገባ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ።

ይህንን ራእይ ለማሳካት

የፀረ-ዘረኝነት ስትራቴጅ የሚከተለውን ያከናውናል፡

  • ዘረኝነትን በማህበረሰብ ስፖርት ውስጥ ለማስወገድ ክልል አቀፍ ዘመቻ ማካሄድ
  • በየቦታው የሚደርሱ የዘረኝነት ክስተቶችን ለመታገል ያለሙ በማህበረሰቡ አባላት የሚመሩ እርምጃዎችን መደገፍ
  • የጥላቻ ንግግርን እና ጠባይን ለማጥፋት የሚያስችሉ ጥበቃዎችን እና ህጎችን ማጠናከር
  • ስለ ዘረኝነት ቅሬታዎችን በበላይነት የሚቆጣጠሩ ድርጅቶች በቀረቡ ቅሬታዎች ሪፖርት እና ምላሽ የሚሰጡበትን መንገድ ማሻሻል
  • ፖሊሶች በስራቸው ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ዘረኝነትን እና የዘር መድልዎን መቀነስ
  • አሠሪዎችና ድርጅቶች ዘረኝነት ከመድረሱ በፊት የሚከላከሉበት እና ከደረሰ በኋላ ምላሽ የሚሰጡበትን መንገድ ማሻሻል
  • ዘረኝነት ላጋጠማቸው ሰዎች ድጋፍ የሚሰጡትን የአካባቢው የፀረ ዘረኝነት ድጋፍ መስጫ ማእከላትን መደገፍ።

ይህ ስትራቴጂ ዘረኝነትን በመቀነስ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ እንገመግማለን እንዲሁም ያመጣውን ለውጥ ለህብረተሰቡ ሪፖርት እናደርጋለን።

ይህ ስትራቴጂ ለምን ያስፈልጋል?

ማህበረሰባችን የተቀላቀለ ነው

  • 30% የሚሆኑት ቪክቶሪያውያን ከአውስትራሊያ ውጭ የተወለዱ ናቸው
  • 8% የሚሆኑት ቀደምት አውስትራሊያውያን ህዝቦች የሚኖሩት ቪክቶሪያ ውስጥ ነው
  • ቪክቶሪያውያን ከ300 በላይ የተለያዩ የዘር መሰረት አላቸው፣ 290 ቋንቋዎች እና ዘይቤዎችን ተናጋሪዎች ሲሆኑ፣ ወደ 200 የሚጠጉ የተለያዩ ሃይማኖቶችን ይከተላሉ

የዘር መድልዎ አሁንም ችግር ነው?

  • በ2022 ከ5ቱ የቀደምት ህዝቦች ውስጥ 3ቱ (60% የሚሆኑት) በአውስትራልያ ውስጥ ዘረኝነት እንዳጋጠማቸው ሪፖርት ተደርጓል
  • በ2023 ከ5 ሰዎች ውስጥ በ1 ላይ (18% የሚሆኑት) በአውስትራልያ ውስጥ ዘረኝነት እንዳጋጠማቸው ሪፖርት ተደርጓል
  • ከ5ቱ አውስትራሊያውያን ውስጥ 3ቱ (63% የሚሆኑት) ከእስያ፣ ከአፍሪካ ወይም ከመካከለኛው ምስራቅ ዘራቸው ለሚመዘዝ ወይም ሃይማኖታቸው ከክርስትና ውጭ በሆኑ ሰዎች ላይ አሉታዊ አመለካከት አላቸው
  • ከ5ቱ አውስትራሊያውያን ውስጥ 3ቱ (62% የሚሆኑት) ዘረኝነትን እንደ 'እጅግ ትልቅ' ወይም 'በተገቢው ሁኔታ ትልቅ' ችግር አድርገው ይመለከቱታል

የመረጃ አለመኖር እና በማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ እምነት ማጣት ዘረኝነት በተገቢው ሁኔታ ሪፖርት እየተደረገ እንዳልሆነ መገመት ይቻላል።

ይህንን ችግር በተመለከት ከማን ጋር ውይይት አደረጋቹህ?

ከቀደምት ህዝቦች፤ ከባለብዙ ባህል እና ባለብዙ ሃይማኖት ማህበረሰባት ውስጥ የተወጣጡ ከ670 በላይ ቪክቶሪያውያን ጋር ተወያይተናል። በእነዚህ ውይይቶች ውስጥ የማህበረሰቡ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ከማህበረሰቡ ጋር የስራ ግንኙነት ያላቸ ሠራተኞች ተካተውበታል።

ቪክቶሪያ ውስጥ ዘረኝነትን ሪፖርት ስለማድረግ

ማንም ሰው የዘረኝነት ጥቃት እየደረሰበት በዝምታ ማለፍ የለበትም። ቪክቶሪያ ውስጥ ዘረኝነትን ወይም የዘር አድልዎ ከደረሰብዎ ወይም ሌሎች ላይ ሲደርስ ካዩ ወደሚከተሉት አካላት ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

የቪክቶሪያ እኩል መብት እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን (Victorian Equal Opportunity and Human Rights Commission)

በሳምንቱ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 10ኤኤም እስከ 2ፒኤም ወደ 1300 292 153 ይደውሉ። ያለክፍያ በነጻ አስተርጓሚ ካስፈለገዎት ወደ 1300 152 494 ይደውሉ።

ኢሜይል enquiries@veohrc.vic.gov.au

በመስመር ላይ መደበኛ ያልሆነ ሪፖርት እዚህ ያድርጉ።

መስማት ለተሳናቸው፣ መስማት ለተቸገሩ ወይም የንግግር ችግር ካለብዎ ከብሄራዊ ቅብብሎሽ አገልግሎት (National Relay Service) ጋር ይገናኙ።

ቪክቶሪያ ፖሊስ

ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት፣ ወንጀል እየተፈጸመ እንደሆነ ሪፖርት ለማድረግ ወይም ፖሊስ ወዲያውኑ በቦታው እንዲገኝ ወደ 000 ይደውሉ።

ድንገተኛ ላልሆኑ ጉዳዮች ወደ ፖሊስ እርዳታ መስመር 131 444 ላይ ይደውሉ ወይም ለነጻ አስተርጓሚ 131 450 ይደውሉ።

በአካባቢዎ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ወይም በመስመር .ላይ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

ማንነትዎን ሳይገልጹ ወደ ክራይም ስቶፐርስ (Crime Stoppers) 1800 333 000 ላይ በመደወል ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

ለተጨማሪ ድጋፍ እና ሪፖርት የማድረጊያ አማራጮችን ለማወቅ፤ እባክዎ የቪክቶሪያን የፀረ-ዘረኝነት ስትራቴጂን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ

ሙሉውን ስትራቴጂ በእንግሊዝኛ ወይም ይህንን መሳይ አጭር መግለጫ በሌሎች ቋንቋዎች መስመር ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ከክልሉ አስተዳዳሪ እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት (Department of Premier and Cabinet ) የለበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ መጀመሪያ ወደ Translating and Interpreting Service (TIS) 131 450 ላይ ደውለው ወደ 03 9651 5111 እንዲደውሉልዎት መጠየቅ ይችላሉ።

በኢሜይል ወደ ክልሉ አስተዳዳሪ እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት (Department of Premier and Cabinet ) antiracism.strategy@dpc.vic.gov.au  መላክ ይችላሉ።

Updated