JavaScript is required
Extreme fire danger is forecast for large parts of Victoria on Thursday 26 December (Boxing Day). Leaving early is always the safest option.
Stay informed at emergency.vic.gov.au

ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten) - አማርኛ (Amharic)

ከስደተኛ ወይም ከጥገኝነት ጠያቂ ዳራ ያለው ከሆኑ፣ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten (ESK)) የሚባል ፕሮግራምም አለ።

ከስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ዳራ ከሆንክ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten (ESK)) ብቁ ልትሆን ትችላለህ። ኢኤስከይ (ESK) በየሳምንቱ ለልጅዎ የሚቻለውን ከፍተኛውን የነጻ መዋዕለ ህፃናትን ሰዓታት እንዲያገኙ ያግዝዎታል።

በ2023፣ የሶስት ዓመት ልጆች መዋዕለ ህፃናት ፕሮግራሞች በየሳምንቱ ከ5 እስከ 15 ሰዓታት እና የአራት ዓመት ልጆች መዋዕለ ሕፃናት ፕሮግራሞች ለ15 ሰዓታት የሚያገለግሉ ናቸው። በኢኤስከይ (ESK) በኩል መመዝገብ በሁለቱም የሶስት አመት እና የአራት አመት ልጅ መዋዕለ ህፃናት በየሳምንቱ ሙሉውን 15 ሰአት እንዲካፈሉ ዋስትና ይሰጣል። ለሚከተሉት ህፃናት አገልግሎት ይሰጣል፦

  • ከስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ዳራ ለመጡ
  • እንደ አቦርጂናል እና/ወይም የቶረስ ስትሬት አይላንደር ነን ለሚሉ
  • ቤተሰባቸው ከልጆች ጥበቃ ድርጅት ጋር ግንኙነት ለነበራቸው

በቪክቶሪያ ውስጥ የትም ቢኖሩ እነዚህ ልጆች ፕሮግራሙ በሚጀመርበት ጊዜ በሳምንት ለ15 ሰዓታት ነፃ መዋዕለ ህፃናት ማግኘት ይችላሉ። አሁን የሚያገኙት እና የሚጠቀሙት ሰዓቶች አይቀየሩም።

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል፡-

ኢኤስከይ (ESK) ብቃት ባለው መምህር በሚሰጡ ሁሉም የመዋዕለ ሕጻናት ፕሮግራሞች ይገኛል። በአቅራቢያዎ ያለ መዋዕለ ሕፃናትን በማነጋገር እና ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ሕጻናት የገንዘብ እርዳታን በመጠየቅ ልጅዎን ማስመዝገብ ይችላሉ። የመዋዕለ ሕፃናት አገልግሎቶች በቋንቋዎ እርስዎን ለመደገፍ ነፃ የትርጉም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

እርዳታ ለማግኘት ወደ ትምሕርት መመሪያው የሶስት አመት እድሜ ልጆች የመዋዕለ ህጻናት መጠየቂያ መስመርን በ1800 338 663 መደወል ወይም የአካባቢዎ ምክር ቤት ማግኘት ይችላሉ። በቋንቋዎ እርዳታ ለማግኘት ወደ ብሄራዊ የትርጉም እና አስተርጓሚ አገልግሎት በ 131 450 መደወል ይችላሉ፣ አስተርጓሚው የአከባቢዎ ምክር ቤት ወይም የትምህርት መመሪያ ቁጥር እንዲደውሉ ይጠይቁት እና አስተርጓሚው በመስመር በመቆየት ያስተረጉምልዎታል።

መቼ ማመልከት እንደሚቻል፡-

ልጆች መዋዕለ ህፃናትን ለመከታተል በተመዘገቡበት ዓመት ከኤፕሪል 30 በፊት ሶስት አመት ከሞላቸው ለኢኤስከይ (ESK) ብቁ ናቸው። 'መቼ መመዝገብ እንደሚቻል' ይመልከቱ።

ልጅዎ አምስት ወይም ስድስት ዓመት ሲሞላው ትምህርት ቤት ይማር እንደሆነ መምረጥ ይችላሉ። ከዚያም በኋላ፣ ሶስት ወይም አራት ዓመት ሲሞላው ኢኤስከይ (ESK)ን ማግኘት ይችላል።

ልጅዎ ለኢኤስከይ (ESK) ብቁ በሚሆንበት ጊዜ ለማስላት እርዳታ ከፈለጉ፣ የትምህርት መምሪያን፣ የአካባቢ ምክር ቤትዎን፣ የወሊድ እና የሕጻናት ጤና ነርስዎን፣ ወይም በአካባቢዎ ያሉ መዋዕለ ሕፃናትን ወይም በአካባቢዎ ካሉት የሚከተሉትን ድርጅቶች ማነጋገር ይችላሉ።

  • የሶስት ዓመት ህፃናት መዋእለ ሕጻናት መጠየቂያ መስመር 1800 338 663
  • ብራዘርሁድ ኦፍ ሰይንት ሎረንስ (Brotherhood of St Laurence) 03 9483 1183
  • ፋውንዴሽን ሃውስ (Foundation House) 03 9389 8900
  • ኤፍካ የህጻናት አገልግሎት (Fka Children’s Services) 03 9428 4471
  • ቪክሴግ ኒው ፊቸርስ (VICSEG New Futures) 03 9383 2533

Updated