JavaScript is required

እንዴት እና መቼ መመዝገብ እንደሚቻል (How and when to enrol) - አማርኛ (Amharic)

ስለ ምዝገባው ሂደት ከአካባቢዎ ምክር ቤት ወይም ከመዋዕለ ሕፃናት አገልግሎት ጋር ይነጋገሩ። እንዲሁም የሶስት አመት እድሜ መዋዕለ ህፃናት መጠየቂያ መስመር በ1800 338 663 መደወል ወይም ወደ 3YO.kindergarten@education.vic.gov.au ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ። የቋንቋ ድጋፍ ወይም አስተርጓሚ ለማግኘት በመጀመሪያ ወደ 131 450 ይደውሉ።

ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten)

ከስደተኛ ወይም ከጥገኝነት ጠያቂ ዳራ የመጡ ልጆች ተጨማሪ ድጋፎችን ማግኘት እና በቅድሚያ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten) ማግኘት ይችላሉ። ልጅዎን በሚያስመዘግቡበት ጊዜ ስለ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten) የአካባቢዎን አገልግሎት መጠየቅ ይችላሉ ወይም ለበለጠ መረጃ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten)ን ይጎብኙ።

መቼ መመዝገብ እንደሚቻል

በቪክቶሪያ፣ ልጆች 3 ዓመት ሲሞላቸው በመዋዕለ ሕጻናት ፕሮግራም መጀመር ይችላሉ። የሶስት እና የአራት አመት መዋዕለ ህፃናትን በየትኛው አመት መጀመር እንደሚችሉ ለማወቅ የልጅዎን የልደት በመጀመሪያ ዕድሜ ማስያ (Starting Age Calculator) ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

የልጅዎ የልደት ቀን በጃንዋሪ 1 እና በኤፕሪል 30 መካከል ከሆነ፣ በየትኛው አመት መዋዕለ ህፃናት እንደሚገባ ለማወቅ ትምህርት የሚጀምርበትን አመት አስቀድመው ማስላት ያስፈልግዎታል። ልጅዎ አምስት ወይም ስድስት ዓመት ሲሞላው ትምህርት ቤት ይማር እንደሆነ መምረጥ ይችላሉ።

የመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ፕሮግራም ማግኘት

የጸደቁ የመዋዕለ ህጻናት ፕሮግራሞችን የሚያቀርቡ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ የመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ፕሮግራም ፈልግ የሚለው ድህረ ገጽን ይጎብኙ (የመዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ፕሮግራም ፈልግ - የትምህርት እና ስልጠና መምሪያ፣ ቪክቶሪያ (vic.gov.au))። የአካባቢዎ ምክር ቤት እና የመዋዕለ ህፃናት አገልግሎቶች በመዋዕለ ህፃናት ውስጥ ቦታ እንዲያገኙም ሊረዱዎት ይችላሉ።

የመዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ምልክትን ይመልከቱ፦

መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ምልክት (Kinder Tick) የቪክቶሪያ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው የተፈቀደ የመዋዕለ ሕጻናት ፕሮግራም እንዲያገኙ ይረዳል።

በአካባቢዎ የመዋዕለ ህፃናት አገልግሎት፣ በአገልግሎቱ ወይም በማዕከሉ ሕንፃ ወይም ግቢ፣ በድረ ገጻቸው ወይም በመረጃ ወረቀታቸው ላይ መዋዕለ ህፃናት (ኪንደር) ምልክት አርማ ይፈልጉ።

Updated