የቪክቶሪያ መንግሥት በአስር ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት የሦስት ዓመት ልጆች መዋለ-ህፃናት ለማስተዋወቅ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ሥራ ላይ እያዋለ ነው - እናም ይህ አሁን በመላው የክልሉ ግዛት ይገኛል፡፡
ይህ ማለት ለቪክቶሪያ ልጆች ሌላ የመማር፣
የማደግ፣ የመጫወት እና ጓደኛ የማፍራት ዓመት ማለት ነው፡፡
ከሶስት አመት ጀምሮ ጥራት ባለው የመዋዕለ ህፃናት መርሃግብር ውስጥ መሳተፍ የልጆችን የመማር፣ የዕድገት፣ የጤና እና የደህንነት ውጤቶችን ከፍ ያደርጋል፡፡
ትናንሽ ልጆች በዙሪያቸው ስላለው ዓለም በጨዋታ መልክ ይማራሉ
በጨዋታ ላይ የተመሠረተ ትምህርት ትናንሽ ልጆች በተሻለ ሁኔታ የሚማሩበት መንገድ ነው። ልጆች አይነህሊናቸውን እንዲጠቀሙ፣ የቋንቋ ችሎታቸውን እንዲገነቡ እና ስለ ቁጥሮች እና ቅጦች እንዲማሩ እድል ይሰጣቸዋል፡፡ እንዲሁም ከሌሎች ጋር እንዴት ተስማምተው መኖር፣ መጋራት፣ ማዳመጥ እና ስሜታቸውን መምራት ወይም መቆጣጠር እንደሚችሉ ይማራሉ፡፡
በቪክቶሪያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ልጆች ለሁለት ዓመት የገንዘብ ወጪው የተሸፈነ የመዋለ-ህፃናት ቆይታን ያገኛሉ
በመላው የክልሉ ግዛት ያሉ ሕፃናት ከ 2022 ጀምሮ ቢያንስ በየሳምንቱ የአምስት ሰዓት የገንዘብ ወጪው የተሸፈነለት የመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብር ተጠቃሚ ይሆናሉ። እስከ 2029 ባለው ጊዜ ውስጥ ሰዓቶቹ በሳምንት ወደ 15 ሰዓታት ይጨምራሉ።
ልጅዎ የሚሄድበት መዋዕለ ህፃናት የትኛውም ይሁን፣ መምህራን እና የሰለጠኑ አስተማሪዎች መርሃግብሩን ይመራሉ
የመዋለ-ህፃናት መርሃግብርን ልጆች የረጅም ወይም የሙሉ ቀን እንክብካቤ (የህጻን እንክብካቤ) በሚሰጡ አገልግሎቶችም ይሁን በተናጥል ባለ መዋዕለ-ህፃናት ውስጥ ሆነው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ትናንሽ ልጆች ስለ ዓለም በጨዋታ አማካይነት ይማራሉ
እንዴት ከሌሎች ጋር ተስማምተው እንደሚኖሩ፣ እንደሚጋሩ፣ እንደሚያዳምጡ፣ እና ስሜታቸውን መምራት ወይም መቆጣጠር እንደሚችሉ ይማራሉ
በመዋዕለ-ህፃናት መርሃግብር ውስጥ፣ ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውን ለመገንባት እና ስለ ቁጥሮች እና ቅጦች ለመማር ጨዋታን ይጠቀማሉ
መምህራን እና አስተማሪዎች ልጆች ጉጉ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው እና ስለ ትምህርት ልበ ሙሉ እንዲሆኑ ይረዳሉ
Updated