ለቤተሰቦች መመሪያ
![Title page on purple background with illustration of two children playing, text displayed is Guide for Families.](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-1.jpg)
ስለ ኪንደር ኪትዎ (Kinder Kit)
ጨዋታ የልጅዎን ትምህርት እና እድገት ለመደገፍ አስደሳች እና አሳታፊ መንገድ ነው። ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እና ቤተሰቦች የዚያ ጉዞ ትልቅ አካል ናቸው።
ኪንደር ኪት (Kinder Kits) በመፅሃፍ፣ ትምህርታዊ መጫወቻዎች እና ለልጅዎ እና ለቤተሰብዎ በቤት ውስጥ እንዲዝናኑባቸው በተዘጋጁ እንቅስቃሴዎች የተሞሉ ናቸው።
እያንዳንዱ ኪንደር ኪት (Kinder Kit) በተለይም ለሶስት አመት ህጻናት እንዲሆኑ ተደርገው የተሰሩ እቃዎችን ያካትታል።
![Illustration of three children playing. One is reading a book, one is colouring in, one is holding animal finger puppets.](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-2.jpg)
የቪክቶሪያ የመጀመርያ ዓመታት (የልጅነት) ትምህርት እና የእድገት ማዕቀፍ (Development Framework)
የልጅነት ጊዜ አስተማሪዎች እና ባለሞያዎች ልጅዎ እንዲያድግ እና እንዲማር ይደግፋሉ።
የመዋዕለ ሕፃናት መርሃ ግብሮች የቪክቶሪያን የመጀመሪያ ዓመታት (የልጅነት) ትምህርት እና እድገት ማዕቀፍ (VEYLDF) ይጠቀማሉ።
በእርስዎ ኪንደር ኪት (Kinder Kit) ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች በእድገት ማዕቀፍ (VEYLDF) ውስጥ ካሉት 1 ወይም ከዚያ በላይ የትምህርት እና እድገት ውጤቶች ጋር ይገናኛሉ፦
- ማንነት
- መማር
- ማህበረሰብ
- የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ
- ደህንነት
ቦርሳ
የ ኪንደር ኪት (Kinder Kit) ቦርሳዎች በየቀኑ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
ልጅዎ የትኛው ቦርሳ የእርሱ እንደሆነ እንዲያውቅ፣ ስዕሎቹን ከኋላ ባለው የካርቶን መለያ ላይ መለማመድ ይችላል።
ቦርሳውን ይክፈቱ እና በ ቬልክሮ (Velcro) መጫኛዎች ይክደኑት። የመጫወቻ ምንጣፉን ለምናባዊ ጨዋታ ይጠቀሙ።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-3.jpg)
- ቦርሳው በልጅዎ ጀርባ ላይ እንዲሆን የቦርሳውን ማሰሪያዎችን ያጥብቁ ወይም ያላሉ
- የመጫዎቻ ተለጣፊዎች ያለው የአትክልት ቦታ ይፍጠሩ
- በስም መለያው ላይ መሳል ያበረታቱ
- የቅድመ-ጽሑፍ ችሎታዎችን ይለማመዱ
ማንበብ
ማንበብ እንደ ቤተሰብ አብሮ ጊዜ ለማሳለፍ ጥሩ መንገድ ነው። የማንበብ እና መጻፍ ክህሎትን ለማሳደግ ከሚረዱ በጣም አስፈላጊ መንገዶች አንዱ ነው።
ከልጅዎ ጋር መደበኛ የታሪክ ጊዜ ማሳለፍ የልጅዎን በምናብ የማሰብ ችሎታ እና የቃላት ክህሎት ለማዳበር ይረዳል።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-4.jpg)
- አንድ ላይ መጽሐፍ ይምረጡ
- ቁጭ ብሎ ለማንበብ ምቹ ቦታ ይፈልጉ
- በታሪኩ ውስጥ ቀጥሎ ሊመጣ ስለሚችለው ነገር ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡ ቦታ ይስጧቸው
- የተለያዩ ድምፆችን ይጠቀሙ
መሳል እና ምልክት ማድረግ
መሳል እና ምልክት ማድረግ ልጆች በፈጠራ ሀሳባቸውን እንዲገልጹ ያስችላቸዋል። በወረቀት ላይ ክሬይኖችን በመሞከር፣ ልጆች፦
- እንዴት እንደሚጻፍ ለመማር ጠቃሚ የሆነውን ጥሩ የእንቅስቃሴ ክህሎቶችን ያዳብራሉ
- የእጆቻቸውን እና የዓይኖቻቸውን ቅንጅት ያሻሽላሉ
- ስለ ቀለሞች፣ ቅርጾች፣ ቅጦች እና መስመሮች ይማራሉ
- የፈጠራ ችሎታን ያሳያሉ
- ከሌሎች ጋር ሃሳብ ይለዋወጣሉ።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-5.jpg)
- ልጅዎን በመሳሉ ሂደት እንዲደሰት ያበረታቱት። መሳል በራስ መተማመንን ለመገንባት ይረዳል
- ስዕል ስትስሉ ተነጋገሩ
- ቀለሞችን እና ቅርጾችን ያስተውሉ እና ይሰይሟቸው
የፈጠራ እንቅስቃሴዎች
የፈጠራ ጨዋታ ሁሉንም 5 የልጅዎን ስሜቶች ያነቃቃል - ማየት፣ ማሽተት፣ መስማት፣ መዳሰስ እና ጣዕምን መለየት። በዙሪያዎ ያለውን አለም ለማሰስ፣ ለማግኘት እና ለመማር አስደሳች መንገድ ነው።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-6.jpg)
- ብሎኮች በሚደረደሩበት ጊዜ የመቋቋም ችሎታን እንዲለማመዱ ያበረታቱ። ከወደቀ፣ ልጅዎ 3 ጥልቅ ትንፋሽ ወስዶ እንደገና መሞከር ይችላል።
- የመጫወቻውን ሊጥ እንደ ኳስ ለማድቦልቦል ይሞክሩ፣ ቅርጾችን ይስሩ፣ ጠፍጣፋ ያድርጉት፣ ይጫኑት።
- አብረው ሙዚቃ ይስሩ። እጆችዎን በማጨብጨብ ወይም በቤት ውስጥ ያሉትን እቃዎች በመነካካት የተለያዩ ዜማዎችን እና ምቶች ይፍጠሩ።
የውጪ ጨዋታ
ክትትል የሚደረግበት የውጪ ጨዋታ የልጅዎ እድገት እና ደህንነት ትልቅ አካል ነው።
ልጆች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- ስለ ተፈጥሮ በመማር ከሳይንስ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሰስ እና ማዳበር
- የነፃነት ስሜት ማሳደግ
- ከሌሎች ልጆች ጋር ማህበራዊ ግንኙነት ማድረግ
- በጨዋታ ጊዜ ጥሩ ምርጫዎችን እንዴት እንደሚያደርጉ ያስሳሉ እና ይማራሉ
- መላውን የሰውነት እንቅስቃሴ፣ የእጅ-ዓይን ቅንጅት እና ትናንሽ የሰውነት ጡንቻዎች ቅንጅት እና እንቅስቃሴ እና የፈጠራ ችሎታዎችን ያዳብራሉ።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-7.jpg)
- ስለ ቅጠሎች ይናገሩ እና የተለያዩ ቀለሞችን እና ቅርጾችን ይሰይሙ
- ዘሮችን አንድ ላይ ይትከሉ
- ከተፈጥሮ ጋር ይገናኙ። አካባቢያችንን ስለመጠበቅ ይነጋገሩ
- የአሸዋ ቤተመንግስት ይገንቡ
ድራማዊ ጨዋታ
ድራማዊ ጨዋታ ልጆች ምናባዊ ታሪኮችን እንዲሰሩ እና የሌሎችን ገፀ-ባህሪያት ሚና እንዲጫወቱ ያበረታታል።
ልጆች ወሳኝ የሆኑ ቋንቋዎችን እና ማህበራዊ ክህሎቶችን ለመለማመድ ድራማዊ ጨዋታን ይጠቀማሉ፣ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፡-
- አዲስ ዓለምን ማሰስ እና መፍጠር
- ማጋራት እና ተራ መጠበቅ
- እርስ በርስ የመገናኘት እና የመደራደር መንገዶች።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-8.jpg)
- እንስሶቹን በእንግሊዝኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች ይሰይሙ
- ገጸ ባህሪያትን ይፍጠሩ
- ታሪኮችን ይፍጠሩ
- የተለያዩ ስሜቶችን ለመመርመር እና ለመግለጽ አሻንጉሊቶችን ይጠቀሙ
ጨዋታዎች
ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ጨዋታዎችን መጫወት የልጅዎን ማህበራዊ ክህሎቶች ለመገንባት ጥሩ መንገድ ነው።
ጨዋታዎች ልጆች የቁጥር፣ የቋንቋ እና ችግር የመፍታት ክህሎቶችን እንዲማሩ ያግዛቸዋል።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-9.jpg)
- የጨዋታ ህጎችን ይማሩ እና ተራ በተራ መጫወት ይለማመዱ
- ችግሮችን የመፍታት እና የማስታወስ ችሎታዎችን ይለማመዱ
- ቁጥሮችን ተወያዩ እና በእቃዎች መቁጠር ተለማመዱ
ማሕበረሰብ መገንባት
ጨዋታ፤ ልጆች ስለ ራሳቸው የሚያውቁበት እና በዙርያቸው ስላለው ዓለም የሚማሩበት መንገድ ነው። ለልጆች፣ መጫወትና መማር እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው። በእርስዎ ኪንደር ኪት (Kinder Kit) ውስጥ ያሉት እቃዎች ስለ ብዝሃነት እና ስለተለያዩ ባህሎች ውይይቶች እንዲያደርጉ ይረዱዎታል።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-10.jpg)
- ስለ ሌሎች ሃገሮች እና ስለ የሃገራቸው እንስሳት ከልጅዎ ጋር ይነጋገሩ።
- የተለያዩ ቋንቋዎች ከየት እንደመጡ ለማየት የዓለምን ካርታ ይመልከቱ።
ማንነትን ማክበር
ልጆች ስለ ሁሉም ባህሎች እንዲማሩ ማበረታታት መግባባትን፣ ተቀባይነትን እና ኩራትን ይገነባል። የአቦርጂናል እና የቶረስ ስትሬት አይላንድ ባህሎች፣ እና እዚህ በቪክቶሪያ፣ የኩሪ ባህሎች፣ ዛሬ ያሉ እና በማደግ ላይ ያሉ ናቸው። በኪትስ ውስጥ እንደ ደራሲዎች እና አርቲስቶች እነሱን ለማክበር ኩራት ይሰማናል። ልጅዎ ስለ ኮሪ ወጎች እና ባህሎች የበለጠ እንዲያውቅ የሚያግዙ አንዳንድ ተግባራት እዚህ አሉ፦
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-11.jpg)
- ለነገሮች ወይም እንስሳት የኩሪ ምልክቶችን ይማሩ
- ስለ ኮሪ ባህሎች፣ መሪዎች እና ጀግኖች ይማሩ እና ይናገሩ
- የሀገርን እውቅና አስፈላጊነት ይወቁ
የቪክቶሪያ አቦርጂናል ትምህርት ማኅበር ድህረ ገጽ የኩሪ ወጎችን እና ባህሎችን የሚዳስሱ አስደሳች፣ አሳታፊ እንቅስቃሴዎች አሉት። ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጹን ይጎብኙ።
በኣውስላን/Auslan የተጻፉ መጻሕፍት
አውስላን በቪክቶሪያ የቅድመ ልጅነት ቋንቋ ፕሮግራም ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል የምልክት ቋንቋ ነው። ይህ ፕሮግራም በአንዳንድ የአራት አመት መዋእለ ህፃናት ውስጥ ይገኛል።
ልጆች ገና በለጋ እድሜያቸው ሌላ ቋንቋ ሲማሩ ብዙ ጥቅሞች አሉት፤ እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- የቅድመ-ንባብ እና ቅድመ-ጽሑፍ ችሎታን መጨመር
- የማገናዘብ ማሰብ ችሎታ እንደ ሁኔታው መለዋወጥ
- በራስ መተማመንን እና ደህንነትን ማሳደግ
- የተጠናቀረ የባህል ማንነት።
በ 2025 ኪንደር ኪትስ ውስጥ የተካተቱት ብዙዎቹ መጽሃፍት ኦውስላን ትርጉሞች አሏቸው።
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-12.jpg)
- ስሜቶችን በአውስላን በኩል ይግለጹ።
- በአውስላን ሰላም ይበሉ።
ደህንነት እና ተጨማሪ ድጋፍ
ሁሉም ልጆች የሚማሩት በተለያየ መንገድና በራሳቸው ፍጥነት ነው። ኪንደር ኪጽ (Kinder Kits) ሁሉንም ችሎታዎች ለመቃወም በተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መጽሃፎችን እና ትምህርታዊ መጫወቻዎችን ለልጅዎ ይሰጣሉ።
እርስዎ ወይም ልጅዎ ተጨማሪ ድጋፍ ከፈለጉ፣ እገዛ በሚከተሉት መንገዶች ይገኛል፦
![](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-13.jpg)
- የቅድመ ልጅነት አስተማሪዎች ለመርዳት ችሎታ እና እውቀት አላቸው። ስለጥያቄዎችዎ የልጅዎን የቅድመ ልጅነት መምህር ያነጋግሩ።
- ባልዎት ጥያቄዎች ላይ ለመወያየት ሀኪምዎን ወይም የእናትና ህጻን ጤና ጥበቃ ነርስን ለማየት ቀጠሮ ይያዙ።
- ነጻ እና ምስጥራዊ የሆነ ምክር እና ድጋፍ ለማግኘት ወደ የወላጅ መስመር/Parentline በ13 22 89 ይደውሉ።
በቅድመ ልጅነት ትምህርት ውስጥ ያሉ ሙያዎች
በቪክቶሪያ እያደገ ባለው የመዋዕለ ሕፃናት ዘርፍ ሥራ ለመጀመር ያስቡበት። እርስዎን የቅድመ ልጅነት መምህር ወይም አስተማሪ እንዲሆኑ ለመደገፍ፣ እነዚህ አሉ፦
- ተለዋዋጭ የጥናት አማራጮች
- ለጋስ ስኮላርሺፕ
- የገንዘብ ማበረታቻዎች።
![Illustration of two children sitting on the floor playing with blocks while two adults talk, speech bubble from one adult with text](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-14.jpg)
የእርስዎን ኪንደር ኪት (Kinder Kit) በመለገስ ላይ
አንዴ ልጅዎ የኪንደር ኪት ዕቃዎቹን እንደጨረሰ፣ ሌላ ሰው እንዲወዳቸው እና እንዲጠቀምባቸው ለበጎ አድራጎት ድርጅት መለገስ ያስቡበት።
አንድ ዕቃ መሰጠት ይቻል እንደሆነ ሲወስኑ ጠቃሚ መመሪያ የሚሆነው፣ ይህንን ለጓደኛ እሰጣለሁን የሚል ነው? መልሱ አዎ ከሆነ ለበጎ አድራጎት መስጠት ተገቢ ነው።
ተስማሚ እቃዎችን መለገስ ለዘለቄታው እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ወሳኝ ነው።
![Illustration of two children adding kinder kit items to a donations box.](/sites/default/files/2025-01/kinder-kit-2025-image-15.jpg)
Updated